ታህሳስ ፴(ሰላሳ ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ርእዮት ዛሬ ሰበር ሰሚ ችሎት ባትቀርብም ጠበቃዋ፣ አባቷ እና ሌሎች የስራ ባልደረቦቿና ጓደኞቿ በችሎቱ ተገኝተው ውሳኔውን ሰምተዋል።
ሰበር ሰሚ ችሎቱ በርእዮት የቀረበው አቤቱታ የህግ ክፍተት የለበትም ሲል ውሳኔ አሳልፎአል።
ጋዜጠኛና መምህርት ርእዮት ጥር 17 ቀን 2004 ዓም በፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት የ14 አመት ጽኑ እስራትና የ33 ሺ ብር ቅጣት እንደተወሰነባት ይታወሳል።
የርእዮት ጠበቃ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም ይግባኝ ያሉ ሲሆን፣ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ውሳኔውን ከ15 አመት ወደ 5 አመት ዝቅ አድርጎት እንደነበር ይታወሳል።
በሰበር ሰሚ ችሎቱ ዛሬ የሰጠው ብይን ትክክል አለመሆኑን የህግ ባለሙያ የሆኑት ርእዮት አባት አቶ አለሙ ደምቦባ ገልጸዋል