ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ላለፉት አራት አመታት የዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን አቋርጠው የነበሩት ኢትዮጵያና ካታር ግንኙነታቸውን እንደገና ለመጀመር ማቀዳቸውን ሱዳን ትሪቢዩን ዘግቧል።
ኢትዮጵያ ከአራት አመታት በፊት ካታር በኢትዮጵያ ውስጥ አፍራሽ ስራዎችን እየሰራች ነው በሚል የዲፐሎማሲ ግንኙነቷን መቋረጧ ይታወሳል።
ኢትዮጵያ ካታር በሱማሊያ የእስልምና አክራሪ ሀይሎችን ትደግፋለች የሚል ተደጋጋሚ ቅሬታ ስታቀርብ ቆይታለች።
የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ የሆኑት አቶ ዲና ሙፍቲ ካታር አዲስ አምባሳደር በያዝነው ወር ወደ አዲስ አበባ ትልካለች ብለው እንደሚጠብቁ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያን ኢምባሲ በዶሀና ለመክፈትም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ቃል አቀባዩ ገልጠዋል።