ጥቅምት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-አዲሱ የ “መለስ አንደበት” የተሰኘው መጽሀፍ በተለያዩ ከተሞች በገበያ ቦታዎች ላይ ሳይቀር እየተዋወቀ ነው።
የአቶ መለስን ፎቶ የለጠፉ መኪኖች በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች እየተዘዋወሩ ህዝቡ መጽሀፉን እንዲገዛ እያግባቡት ነው።
መጽሀፉ አቶ መለስ ስልጣን ከያዙበት ከ1983 ዓም ጀምሮ ያደረጉዋቸውን ንግግሮች የሚተነትን ነው።
” መለስና ውጤታማ ጉዞዋቸው” በሚለው ክፍሉ ውስጥ አቶ መለስ የማርክሲዝም ሌኒኒስት ንድፈ ሀሳብን ከፈጣሪዎቹ ከእነ ማርክስ እና ሌኒን እኩል እንደሚያቁት፣ ከእነሱም በተሻለ እንደገለጡት፣ የአብዮታዊ ዲሞክራሲን ፍልስፍና የነደፉና ህወሀትን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመቀላቀል ኢህአዴግን የመሰረቱ መሆናቸውን ያትታል።
በጋዜጠኛ አለሜ ቡቃያ የተጻፈውና የ60 ብር ዋጋ የተተመነለትን መጽሀፍ መንግስት በሚፈልገው መጠን ሊሸጥ እንዳልቻለም ታዛቢዎች ገልጠዋል።