የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ መታፈኑን ስለመግለጽ

ግንቦት 21/ 2002 ዓ/ም
የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን /ኢሳት/ ምንጩን በዉል ለማወቅ አዳጋች በሆነ ሞገድ /electronic interference/ በመጠቃቱ
የስርጭት አገልግሎቱን ከአለፉት ሦስት ቀናት ጀምሮ ለተመልካቹ ለማድረስ አለመቻሉ ይታወቃል ። የአገልግሎት ሰጪው ድርጅት ባደረገው የቅድመ ማጣሪያ
ስራም የሚከተሉትን እውነታዎች ለማረጋገጥ ተችሏል፣
አገልግሎቱን የሚሰጠዉ ኩባንያ ችግሩን ለመፍታት ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ሲያደረገ ከቆየ በሁዋላ የኢሳት ስርጭት ምንጩ በውል ካለታወቀ አካባቢ በሚሰራጭ
ሞገድ ኢላማ ተደርጎ እየተጠቃ መሆኑን ለማረጋገጥ ችሎአል።

ኩባንያው ችግሩን ከለየ በሁዋላ ተገቢዉን የማስተካከያ እርምጃ የወሰደ ቢሆንም፣ ከ72 ሰዓታት በኋላ ጣልቃ ገቡ ሞገድ ተጠናክሮ በመምጣቱ የኢሳት ስርጭት
በድጋሚ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

ኢሳት ለተመልካቾቹና ለደጋፊዎቹ ሁለንተናዊ ድጋፋቸዉን እንዲለግሱት ጥሪ እያቀረበ፣ የኢሳት ማኔጅመንት ለተመልካቾችና ለደጋፊዎች የገባዉን ቃል ኪዳን ለማሳካት
የማይፈነቅለዉ ድንጋይ እንደማይኖር ለማረጋገጥ ይወዳል።

የኢሳት ማኔጅመንት ለተጨማሪ ማብራሪያ [email protected] ይጻፉ