ነሀሴ ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- አዲሱ የግብጽ መሪ፣ ሙሀመድ ሙርሲ በኢራን በሚካሄደው የገለልተኛ አገሮች ጉባኤ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት የሶሪያ ተቃዋሚዎች የሚያካሂዱትን ትግል መደገፍ የሞራል ግዴታ ነው ።
የሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዋሊድ ሙአለም የፕሬዚዳንት ሙርሲ ንግግር ” በሶሪያ የሚካሄደውን ደም ማፈሰስ ይበልጥ የሚያባብስ ነው” ብለዋል።
120 አባላት ባሉት በዚህ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንት ሙርሲ ሲናገሩ ” የሶሪያ ህዝብ በጨቋኝ መንግስቱ ላይ የሚያደርገው ትግል የሞራል ግዴታ ብቻ ሳይሆን የፖለቲካና የስትራቴጂክ ጠቀሜታ አለው።” ብለዋል።
ፕሬዚዳንቱ የጉባኤ አባላቱ በመላ የሶሪያን ህዝብ እንዲደግፉ ጥሪ አቅርበዋል።
የግብጹ መሪ የሶሪያ መንግስት ዋነኛ ደጋፊ በሆነቸው ኢራን ተገኝተው ያደረጉት ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ሆኗል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide