አዲስ አበባ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ በከፍተኛ የጸጥታ ቁጥጥር ስር ትገኛለች ተባለ::

ነሀሴ ፳፬ (ሀያ አራት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ዘጋቢያችን እንደገለጠው በዛሬው እለት እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት በከተማዋ የተለያዩ ክፍሎች ተሰማርተው የጸጥታ ስራ እየሰሩ ነው።

የጸጥታ ቁጥጥሩ እንዲጠናከር የሆነበትን ትክክለኛ ምክንያት ለማወቅ ባይቻልም በአንድ በኩል የሙስሊሙ ማህበረሰብ በነገው እለት ተቃውመ ያነሳል በሚል ፍርሀት ወይም በሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በመስቀል አደባባይ የሚካሄደው የአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ የሽኝት መርሀግብር እንዳይደናቀፍ ለማድረግ ታስቦ ሊሆን እንደሚችል ግምቱን አስፍሯል።

ሙስሊሙ ማህበረሰብ በነገው እለት ተቃውሞውን ይቀጥል አይቀጥል እስካሁን የታወቀ ነገር የለም። ይሁን እንጅ የአቶ መለስ ዜናዊ ግብአተ ምድር እንደተፈጸመ ተቃውሞው እንደሚቀጥል የኢሳት የመረጃ ምንጮች ገልጠዋል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide