ሚያዚያ ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በአፋር ክልል ካቢኔ ውስጥ የተነሳው ውዝግብ አይሎ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ እስማኤል አሊ ሴሮ ፣ የብአዴፓን የፖለቲካ ጉዳይ ሃላፊን ከሀላፊነት አንስተዋል።
ሌሎች የካቢኔ አባላት በበኩላቸው ” ፕሬዚዳንቱ ” ላለፉት 18 አመታት በስልጣን ላይ ቆይተው፣ ለክልሉ ህዝብ ያመጡት ነገር ባለመኖሩ ስልጣናቸውን መልቀቅ አለባቸው” እያሉ ነው። አብዛኞቹ የካቢኔ አባላት ፕሬዚዳንቱ የሀወሀት ጉዳይ አስፈጻሚ በመሆን የአፋርን ህዝብ ለጥቃት ዳርገውታል የሚል ክስ እንደሚያቀርቡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ በበኩላቸው እርሳቸውን ከስልጣን ለማስነሳት የሚሞክሩት “የስልጣን ጥም ያለባቸው ነው” በማለት ስልጣናቸውን ለመልቀቅ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ግለጸዋል።
ውዝግቡ አሁንም መቋጫ ሳይገኝ እንደቀጠለ ሲሆን፣ የፌደራል መንግስት በክልሉ እየተስፋፋ ከመጣው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ ፕሬዚዳንቱን ከስልጣን በማውረድ ሌላ ሰው ሊሾም ይችላል የሚሉ ግምቶች አሉ።