ፖሊሶች በግድግዳ ላይ የሚጻፉ ጽሁፎችን ተከታትለው እንዲያጠፉ ታዘዙ

መጋቢት ፳፪(ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በከተማዋ የተለያዩ አካባቢዎች በግድግዳዎች ላይ ተጽፈው የሚገኙ የተለያዩ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው ጽሁፎች በአስቸኳይ እንዲጠፉ  የደህንነትና ድርጅት ጉዳይ ጽ/ቤት ለአዲስ አበባ ፖሊስ ትእዛዝ ሰጥቷል። ፖሊሶቹ በግድግዳ ላይ የተጻፉ የነፃነትና የፍትህ ጥያቄዎችን  የሚያቀርቡ የግድግዳ ላይ ጽሁፎችን እግር በእግር ተከታትለው ማጥፋት እንዳለባቸው ተነግሯቸዋል፡፡ ትእዛዙን ተከትሎም የአዲስ አበባ ፖሊሶች በየቀጣናው እየተዘዋወሩ ጽሁፎችን በማጥፋትና በመደለዝ ስራ ላይ ተጠምደዋል፡፡ አንዳንድ ጽሁፎች በቀላሉ በማይጠፉ ቀለሞች የተጻፉ በመሆናቸው  ጽሁፎችን ለማጥፋት ፖሊሶች ሲቸገሩ ተስተውሎአል።

በአዲስ አበባ ሃይማኖታዊና ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸው የተቃውሞ ጽሁፎች በየጊዜው በግድግዳዎች ላይ እንደሚጻፉ ይታወቃል።