ነሃሴ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአገራቸውን ወሳኝ ፖለቲከኞች ድጋፍ ያገኙት ፕሬዚዳንት ኦባማ፣ አለማቀፍ ድጋፍ ለማግኘት የሚያደርጉትን ዘመቻ ዛሬ በስዊድን ጀምረዋል።
አለም ያስቀመጠው ቀይ መስመር አለ፣ያም መስመር ” የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን መጠቀም አይቻልም” የሚል ነው፤ አለም ለዚህ ውሳኔው በጋራ ሊቆም ይገባል ብለዋል ፕሬዚዳንቱ።
ከአውሮፓ አገራት መካከል እስካሁን ድረስ ለአሜሪካ እርምጃ ድጋፏን የገለጸችው ፈረንሳይ ብቻ ናት።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን አሜሪካ የጸጥታው ምክር ቤትን ውሳኔ ሳታገኝ የምትስደውን እርምጃ እንደማይደግፉ ተናግረዋል።
ፕሬዚዳንቱ የአሜሪካን ድርጊት ለመቃወም ስለሚወስዱት እርምጃ ግን የተናገሩት ነገር የለም።