ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆኑ

(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 6/2010)

የሕወሃቱ እጩ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመረጡ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለምርጫ ከቀረቡለት 3 እጩዎች የሕወሃቱን እጩ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃናን የአዲስ አበባዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት አድርጎ መርጧል።

ለምርጫ የቀረቡት 3 እጩዎች ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ፣ዶክተር ደይሉ ኡመርና ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና ነበሩ።

ለአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንትነት 21 ምሁራን ለውድድር ሲቀርቡና ከመካከላቸው 9ኙ ሲመረጡ ሕወሃት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃናን ለመሾም ደባ እየተፈጸመ መሆኑን ኢሳት ቀደም ብሎ መዘገቡ ይታወሳል።

በዚሁም መሰረት በመጨረሻ ከኦሕዴዱ እጩ ፕሮፌሰር በቀለ ጉተማ ጋር ለምርጫ የቀረቡት የሕወሃቱ ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እንዲሆኑ በትምህርት ሚኒስቴር ተሹመዋል።