ጥር ፭(አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፎርቹን ሳምንታዊ ጋዜጣ እንደዘገበው፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ -የአእምሯዊ ንብረት ጽህፈት ቤትን በጀነራል ዳይሬክተርነት እረየመሩ ያሉትን አቶ ብርሀኑ ያዴሎን ካለፈው ታህሳስ 27 ቀን ጀምሮ ከስልጣን አንስተዋቸዋል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተጻፈ ደብዳቤ ከዚያው እለት ጀምሮ በአስቸኳይ አቶ ብርሀኑ ያዴሎ ከስልጣናቸው መነሳታቸውንና በምትካቸው በቢሮው የፓተንት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ግርማ በጅጋ መተካታቸውን ይገልጻል።
አቶ ብርሀኑ ያዴሎ የደኢህዴግ አባል ሲሆኑ፤ በምትካቸው የተሾሙት አቶ ግርማ በጂጋ ደግሞ የኦህዴድ አባል ናቸው።
አንጋፋ የኢህአዴግ አባል የሆኑትና በአቶ መለስ ጊዜ ወቅት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት ሀላፊ፣ ቀጥሎም የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር የነበሩት አቶ ብርሀኑ ያዴሎ፤ በ2002ቱምርጫ በቦን ተፎካጃሪያቸው ከነበሩት ከዶክተር አሸብርረ ወልደጊዮርጊስ ጋር ከፍተኛ እስጥ እገባ ውስጥ ገብተው እንደነበር ይታወቃል። የጸረ ሽብር ህጉንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችን ለማገድ የወጣውን አዋጅ ካረቀቁት የመንግስት ባለስልጣናት መካከል አንዱ አቶ ብርሀኑ ያዴሎ ናቸው።