ከደምሕት ጋር ግንኙነት አለህ ተብሎ  የታሰረው ወጣት ሺሻይ አዘናው ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት

ጥር ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከትግራይ ሕዝብ ዲሚክራሲያዊ ድርጅት ‹‹ደሚህት››  ጋር ግንኙነት  ተብሎ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተበት የአንድነት የመቀሌ ዞን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ፤ ወጣት ሺሻይ አዛናው በትናንትናው ፍርድ ቤት ቀርቦ ተጨማሪ ቀጠሮ ተጠየቀበት።

ወጣት ሲሳይ  ቀደም ሲል በተጠየቀበት የሃያ ስምንት ቀናት ቀነ-ቀጠሮ መሰረት ትናንት በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት   ቢቀርብም፣ ፖሊስ ማስረጃዬን ሰብስቤ አልጨረስኩም በማለት   እንደገና የሃያ ስምንት ቀናት ተጨማሪ ግዜ ይሰጠው ዘንድ ጠይቋል፡፡

ጠበቃ አቶ ገበየሁ ይርዳው፣ ‹‹ፖሊስ ያቀረባቸው ምክንያቶች የህግ አግባብ  እንደሌላቸው በማስረዳት፣ የደንበኛቸው ዋስትና መብት  ይከበርለት ዘንድ ቢጠይቁም፤ ፍርድ ቤቱ የፖሊስን ተጨማሪ ግዜ ጥያቄ በመቀበል፣  ለየካቲት 4 ቀን 2007  ተለዋጪ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

ወጣት ሺሻይ አዛናው፣ ከሁለት ወራት በላይ ዋስትና መብታቸው ተነፍጎና አንዳች ማስረጃ ሳይቀርብባቸው በእስር ላይ ይገኛል፡፡

<<ህገ-መንግስቱ ይከበር፣ ኑ ኢትዮጰያዊ ህልም እናልም>>በማለታቸው የፈጠራ የሽብርተኝነት ክስ የተመሰረተባቸው የዞን 9 ጦማርያንና ጋዜጠኞች በፍርድ ቤት ለ 15ኛ ጊዜ መቀጠራቸው ይታወቃል።