ታህሳስ ፳፱(ሃያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ግንቦት7 የፍትህ፣ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ህወሀት መራሹ መንግስት በሀረር
በታዳጊው ላይ የወሰደውን ኢሰብአዊ ድርጊት በጽኑ አውግዟል።
ዜጎች መብታቸውን በጠየቁ በጥይቅ የቆላሉ ያለው መግለጫው፣ ከእንዲህ አይነት አስከፊ ስርአት ለመላቀቅ መላው ኢትዮጵያውያን ከሙስሊም ኢትዮጵያውያን የትግል ጽናት በመማር ለእውነተኛ የስርአት ለውጥ እንዲነሱ ጥሪ አቅርቧል።
ህወሀት መራሹ መንግስት ቅንጣት ያህል ለዜጎች መብት መከበር ደንታ የሌለው ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ህይወትን በመቅጠፍ፣ በስልጣኑ የሚመጣበትን ለመመከት ማናቸውንም ወንጀሎች ከመፈጸም እንደማይመለስ ለማሳየት የአርፋችሁ ተቀመጡ መቀጣጫ ይሆን ዘንድ ህጻናትን በመግደል የአውሬነት ባህሪውን ቀጥሎበታል የሚለው ግንቦት7 ፣ ብቸኛው መፍትሄ በጽናት መታገል መሆኑም አስምሮበታል።
በተመሳሳይ ዜና በአለፈው አርብ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ያደረጉትን ተቃውሞ ተከትሎ በደቡብ ወሎ በርካታ ሙስሊሞች መታሰራቸው ታውቋል።
የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት የጸጥታ ሀይሎች በጥቆማ ቤት ለቤት እየዞሩ በርካታ ወጣቶችን በደሴና አካባቢዋ በሚገኙ ቀበሌዎች ይዘው አስረዋል።