መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሙርሲ ስልጣናቸውን በሀይል ከተነጠቁበት ጊዜ ጀምሮ ግብጽ ሰላም ማግኘት አልቻለችም። የአገሪቱ መንግስት የፕሬዚዳንት ሙርሲን ደጋፊዎች ለማደን በሚያደርጉት ጥረት አንድ የፖሊስ ጀኔራል ተገድለዋል።
መንግስት በርካታ የፕሬዚዳንቱን ደጋፊዎች በቁጥጥር ስር ማዋሉን ሲያስታውቅ፣ ደጋፊዎቹ ግን ራሳቸውን መሰራያ በማስታጠቅ መንግስት ለመፋለም ቆርጠው መነሳታቸው ይነገርላቸዋል።
መንግስት በያዘው አቋሙ ከገፋበት ግብጽ ዳግም ሶሪያ ልትሆን እንደምትችል ምሁራን ይናገራሉ።
ከሁለት አመት በፊት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክን በማውረድ የተጀመረው የግብጽ የዲሞክራሲ ትግል ሂደት መጨናገፉን የሚገልጹት ምሁራን፣ በአሁኑ ሰአት የመንግስት ዋና አጀንዳ ሰላምን ማረጋገጥ ነው ይላሉ።