ኢሳት ዜና:- (Aug. 28) ኢሳት የማረሚያ ቤቱን ምክትል አዛዥ በመጥቀስ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንደማይጎበኝ በዘገበ በሁለተኛው ቀን የመጎብኘት እድል ማግኘቱን ለማወቅ ተችሎአል።
ከሃሙሱ የችሎት ውሎ በኋላ ወደ ቃሊቲ የተላከው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ዞን አራት ተብሎ በሚጠራውየእሥረኞች ክፍል ውስጥ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ተመስገን ከጓደኞቹ ጋር ለ 10 ደቂቃዎች እንዲያወራ ቢፈቀድለትም፣ ሰለምታዎችን ከመለዋጥ በስተቀር ስለ እስሩ ሁኔታ ዝርዝር መረጃ ለመስጠት አልቻለም።
አለማቀፍ ድርጅቶች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዲፈታ ከፍተኛ ውትወታ እያደረጉ ይገኛሉ።
______________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide