ግንቦት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሀላፊ ጆን ኬሪ በአዲስ አበባ ከጠቅላይ ሚኒሰትር ሀይለማርያም ጋር ተወያይተዋል።
ኬሪ በኢትዮጵያ በሚታየው ሰብአዊ መብቶች ጥሰት ዙሪአ ከአቶ ሀይለማርያም ጋር ስለመነጋገራቸው የተገለጸ ነገር ይለም። ባለስልጣኑ የኢህአዴግ መንግስት የህዝብን መብቶች እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉ የተለያዩ አለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅቶች ሲወተውቱ ከርመዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ 50ኛው አመት የአፍሪካ ህብረት በአል በሚከበርበት እለት በአብዛኛው የአገሪቱ ክፍል መብራት መጥፋቱን የሚደረሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።