(ኢሳት ዲሲ–ሕዳር 11/2011) በኢትዮጵያ አሁን የተገኘው ለውጥ በሁሉም ህዝብ ትግል የመጣ በመሆኑ እኛም ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ አርአያነታችንን ማስመስከር ይገባናል ሲሉ ጀነራል ሰዓረ መኮንን ገለጹ።
የኢትዮጵያ የሃገር መከላከያ ሚኒስቴር ጠቅላይ ኤታማጆር ሹም ጄነራል ሰዓረ መኮንን በአንድ የውይይት መድረክ ላይ እንደገለጹት በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ የሁሉንም ሕዝብ ተሳትፎ የጠየቀ በመሆኑ ሰራዊቱም የዚህ ለውጥ ተጠቃሚ እና ደጋፊ ነው ።
በለውጡ የሰራዊቱን ኑሮ ከማሻሻል ጀምሮ ለአከባቢው ሰላም የነበረን ሚና ተጠናክሮ እንዲቀጥል አቅጣጫ መቀመጡንም ገልጸዋል።
እናም ከለውጡ ጋር መሄድና የዘመናዊ ሰራዊት ግንባታን ማፋጠን ይገባናል ብለዋል።
ጠቅላይ ኢታማጆር ሹም ሰዓረ መኮንን እናደሉት የኢትዮጵያ ሕዝብ በትግል ላገኘው ለውጥ መከላከያ ሰራዊቱ አጋርነቱን ያረጋገጣል።
እኛ ለሕዝባችን የመጨረሻ ምሽግ ነን ሲሉም ሰራዊቱ ከለውጡ እና ከሕዝቡ ጋር መቆሙንም አረጋግጠዋል።