ሰኔ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የፌደራል መንግስቱ አዋሳን በስሩ ለማድረግ እቅድ እንዳለው ሲታወቅ፣ የሲዳማ ዞን በበኩሉ ድርጊቱን ይቃመዋል። በቅርቡ በተደረገው ውይይት ላይ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር፣ የሲዳማ ዞን ባለስልጣናትም የፌደራል መንግስቱ ባለስልጣናት የሚመሩትን ስብሰባ ረግጠው መውጣታቸውንና ጉዳዩን ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እውቅና ውጭ እያካሄዱት ነው።
አዲሱ ውዝግብ የአዋሳን ህዝብ ትኩረት መያዙም ታውቋል። በ1994 ኣም በፌደራል መንግስትና በዞኑ መካከል በተፈጠረው አለመግባባት ከ40 እስከ 100 የሚደርሱ የሲዳማ ተወላጆች መገደላቸው ይታወሳል።
የመለስ መንግስት ከፍተኛ የህዝብ እልቂት ያስከተለውን የቆየ ችግር መልሶ በማምጣት ሌላ ችግር ለመፍጠር ለምን እንደተነሳሳ ግልጽ የሆነ ነገር የለም ይላሉ የአካባቢው ነዋሪዎች።
በሌላ ዜና ደግሞ በወላይታ ዞን የሚኖሩ መምህራን በአዲስ ራእይ ላይ በወጣ ጽሁፍ ውይይት ለማድረግ በሚል ለአንድ ሳምንት ትምህርት እንዲዘጋ መደረጉ በመምህራን እና በተማሪዎች ተቃውሞ ቀርቦበታል። በፈተና ወቅት ለመምህራን የፖለቲካ ስልጠና በመስጠት ትምህርት እንዲዘጋ ማድረጋቸውን መምህራን እና ተማሪዎች ቢገልጹም በመንግስት በኩል ግን ምንም አይነት የማስተካከያ እርምጃ አልተወሰደም።
በሌላ በኩል ደግሞ በዚሁ ከተማ አንድ የጋዜጣ አዟሪ በፖሊስ ተይዞ እስር ቤት ገብቷል። ጋዜጣ አዟሪው ፍትህ ጋዜጣን ሲያሰራጭ በነበረበት ጊዜ መያዙን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ከዚህ ቀደም የግል ጋዜጣ እንዳይሸጥ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲሰጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሎአል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide