የጥቅምት ወር የዋጋ ግሽበት ወደ 15 ነጥብ 8 በመቶ ዝቅ ማለቱ ተነገረ

ህዳር 5 (አምስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የማእከላዊ ስታትስቲክስ እጀንሲ እንዳለው ያሳለፍነው ወር የዋጋ ግሽበት ከመስከረም ወር ጋር ሲነጻጸር 0 ነጥብ 7 ቀንሷል።

ለዋጋ ግሽበቱ መቀነስ የምግብ ሸቀጦች መቀነስ አስተዋጽኦ አድርጓል

የምግብ ሸቀጦች ዋጋ ላለፉት ስምንት ተከታታይ ወራት የቀነሰ ሲሆን ፥ መስክረም ወር ላይ 17 ነጥብ 6 በመቶ የነበረው የምግብ ዋጋ  በጥቅምት ወር ወደ 13 ነጥብ 2 በመቶ መውረዱ ተገልጿል።

ይሁን እንጅ የኢትዮጵያ ህዝብ አሁንም መኖር አልቻልንም በማለት በተደጋጋሚ ምሬቱን እያሰማ ነው።