ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአንድ አመት ያክል ተቋርጦ የነበረው የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት እንደገና ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን አስታውቀዋል። ድርድሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ለድርድር ቢቀመጡም እስካሁን ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሊያመጡ አልቻሉም።
የኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደሚሉት በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እየሻከረ ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳንም የድርድሩ ቦታ ከአዲስ አበባ እንዲወጣ ተፈልጋለች። ደቡብ ሱዳን ውስጥ ለውስጥ በአገርዋ የነበሩ በንግድ ስራና በስለላ ላይ የተሰማሩ የህወሃት የደህንነትና የጦር መኮንኖችን ከአገሩዋ እያስወጣች ነው።
የኢህአዴግ መንግስት በበኩሉ ደቡብ ሱዳን ውስጥ ያለው የዩጋንዳ ጦር ከአገሪቱ እንዲወጣ ይፈልጋል።