የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገሪቱ የሚካሄደውን ጦርነት በመሸሽ በእየቀኑ እስከ 1 ሺ ሰዎች በጋምቤላ አካባቢ ወደ ሚገኙ የኢትዮጵያ ግዛቶች እየገቡ ነው። ስደተኞቹ ረጅሙን መንገድ በማቋረጣቸው በምግብ እና በውሃ እጥረት የተጎዱ መሆናቸውን የጋምቤላ አካባቢ ነዋሪዎች ይናገራሉ።

እልባት ያልተገኘለት የደቡብ ሱዳን ጦርነት በሚቀጥሉት ቀናት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከአገሪቱ የሚወጡ ዘገባዎች ያመለክታሉ።የደቡብ ሱዳን መንግስት ሰሞኑን የነዳጅ ከተማ የሆነቸውን ቤንትዩን የተቆጣጠሩት በሱዳን መንግስት ከሚሰለጥኑ የጃንጃዊድ ሚሊሺያ አባላት ጋር በመሆን ነው ሲል የሳልቫኪር መንግስት ገልጿል። የሱዳን መንግስት ግን እጁ እንደሌለበት እይገለጸ ነው።

ከተማዋን ለማስለቀቅ ተከታታይ ጥቃት እንደሚፈጽምም መንግስት አስታውቋል። አዲስ አበባ ላይ ሲካሄድ የነበረው ድርድር ውጤት አልባ መሆኑን የሚገልጹት ዘገባዎች ፣ የአሜሪካ መንግስት በሁለቱም ተፋላሚ ሃይሎች ላይ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት ቢያስፈራራም ማስፈራሪያው እስካሁን ውጤት አላስገኘም።