መጋቢት ፲፯ (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኬንያ ይህን ህግ ያወጣችው የሶማሊያ ስደተኖች የጸጥታ ችግር ፈጥረውብኛል በሚል ነው። ሁሉም የሶማሊያ ስደተኞች ካኩማ እና ደደሃብ ወደሚባሉት የስደተኞች ካምፖች እንዲገቡ ይህን ባማያደረጉ ስደተኞች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ መንግስት ገልጿል።
አለማቀፍ ተቋማት ተቃውሞቸውን እየገለጹ ቢሆንም፣ የኬንያ መንግስት ግን በውሳኔው ለመጽናት የቆረጠ ይመስላል። በኬንያ በአልሸባብ የሚቀነባበሩ ፍንዳታዎች የበርካታ ንጹሃን ዜጎችን ህይወት መቅጠፉ ይታወቃል። አገሪቱ ጦሯን በሶማሊያ ማሰማራቱዋን አልሸባብ በጽኑ ይቃወማል።
ከ600 ሺ ያላነሱ የሶማሊያ ዜጎች በደደሃብና ካኩማ ካምፖች ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙ ዘገባዎች ያመለክታሉ።