የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት መውረዱን ብሉም በርግ ዘገበ

ሐምሌ ፪ (ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ብሉምበርግ ብሄራዊ ስታትስቲክስን ጠቅሶ እንደዘገበው በሰኔ ወር ውስጥ የዋጋ ንረቱ ከ25 በመቶ ወደ 21 በመቶ ዝቅ ብሎአል። የምግብ ዋጋዎች በአንጻሩ ከአምናው ጋር ሲተያይ 21 በመቶ ከፍ ብሎአል።

የአቶ መለስ መንግስት በሰኔ ወር የዋጋ ንረቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርደው ተናግሮ ነበር። ይሁን እንጅ አቶ መለስ ይህን ማድረግ እንደማይቻል አምነው በመስከረም ወር ግሽበቱን ወደ አንድ አሀዝ እንደሚያወርዱት ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

የአለማቀፍ የገንዘብ ተቋማት  የኢትዮጵያ የዋጋ ንረት ከአለም አገራት ጋር ሲተያይ አሁንም ከፍተኛ ነው ይላሉ።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide