ሚያዚያ ፳፭ (ሃያ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ለኢሳት የደረሰው ዜና እንደሚያመለክተው ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ሺኚዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ መከልከላቸውን ኢሳት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን፣ እግዱ አሁንም አለመነሳቱን ለማወቅ ተችሎአል።
መንግስት ለአየር መንገድ ሰራተኞች እገዳው የተጣለው የሽብርተኝነት ጥቃት እንደሚፈጸም መረጃ ስለደረሰኝ ነው ቢልም፣ አንዳንድ ወገኖች ግን የመንግስትን ምክንያት አልተቀበሉትም። እነዚህ ወገኖች እንደሚሉት ዋነኛው ምክንያት መንግስት በሺዎች የሚቆጠሩ ሴት የቤት ሰራተኞችን ወደ ሳውዲ አረብያ እየላከ መገኘቱ እንዳይታወቅበት ነው። እነዚህ ወገኖች በቪዲዮ አስደግፈው በላኩት መረጃ ላይ እንዳመለከቱት መንግስት በጸጥታ ስም ህዝቡ ወደ አረብ አገራት የሚጎርፉትን ወጣቶች እንዳይመለከት እና ትችት እንዳይቀርብበት ለማድረግ ሆን ብሎ የፈጠረው ዘዴ ሊሆን ይችላል ይላሉ።
በአሁኑ ጊዜ 45 ሺ የሚጠጉ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች በቤት ሰራተኛነት ወደ ሳውዲ አረቢያ እየተላኩ ነው። ወጣቶችን ወደ ሳውዲ የሚልኩት ደግሞ ከመንግስት ጋር በሽርክና የሚሰሩት የህወሀት ሰዎች ናቸው። ጉዳዩን በቅርብ የታዘበው ዘጋቢያችን እንደሚለው ደግሞ ፓስፖርት ለማውጣት ወደ ኢሚግሬሽን ጽህፈት ቤት የሚሄዱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር በአስደንጋጭ ሁኔታ እየጨመረ ነው። ወደ ሳውዲ የሚሄዱ አትዮጵያውያን በ10 ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ጉዳዩን ለሚያስፈጽሙ ባለስልጣናት እንደሚከፍሉ ይታወቃል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide