ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ከቻይና ጉዋንዙ ግዛት የተነሳው የበረራ ቁጥሩ ኢቲ 607 አውሮፕላን በህንድ የሙምባይ ግዛት በድንገት አርፎ ነዳጅ መቅዳቱ ተዘግቧል። ይሁን እንጅ ከ3 ሰአታት ቆይታ በሁዋላ እንደገና በረራውን የጀመረው አውሮፕላን ከአንድ ሰአት ተኩል በረራ በሁዋላ ዳግምበሙምባይ አየር ማረፊያ ለማረፍ ተገዷል።
በውስጡ 283 መንገደኞችን፣ 14 የበረራ አስተናጋጆችንና ሰራተኞችን የያዘው አውሮፕላን ያጋጠመው የቴክኒክ ችግር በውል ተለይቶ አልታወቀም። አውሮፕላኑ ጥገና እየተደረገለት ሲሆን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በጉዳዩ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።