ግንቦት ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሳተላይት ሬዲዮ ማኔጅመንት ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ መሰረት በዩናይትድ ኪንግደም፣ በጀርመን፣ በደቡብ አፍሪካና በኖርዌይ አድማጮች የኢሳት ሬዲዮን ፕሮግራሞች በስልክ እንዲያዳምጡ የሚያስችል አገልግሎት ዘርግቷል።
በዚህ መሠረት በዩናይትድ ኪንግደም የሚገኙ የኢሳት ሬዲዮ አድማጮች በስልክ ቁጥር 44-203-519-7144፣ የጀርመን አድማጮች 49-230-218-590-0200፣ የደቡብ አፍሪካ አድማጮች 27-105-918-884፣ የኖርዌይ አድማጮች ደግሞ በስልክ ቁጥር 47-219-532-14 ደውለው ፕሮግራሞችን ማድመጥ የሚችሉ መሆኑን የኢሳት ማኔጅመንት አስታውቋል።
ከዚህ በፊት በካናዳና በዩናይትድ ስቴትስ በስልክ በመደወል የኢሳት የሬዲዮ ፕሮግራሞችን ማድመጥ የሚያስችል አገልግሎት የነበረ ሲሆን አሁን የተጨመሩትን የ4 አገሮች የስልክ የሬዲዮ አገልግሎት ጨምሮ በስድስት ሀገሮች ኢሳት ሬዲዮ በስልክ መስማት ተችሏል።
የኢሳት የአይ.ቲ. ዲፓርትመንት ኢትዮጵያ የኢሳት ሬዲዮ በስልክ በመደወል በነፃ እንዲሰማ የማድረግ የቴክኒክ ሥራ እየሠራ መሆኑን ያመለከተው የኢሳት ማኔጅመንት መግለጫ ይህም በቅርቡ እውን ይሆናል የሚል እምነት እንዳለው አስታውቋል።