ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሸንጎው ከፍተኛ የአመራር ምክርቤትቅዳሜ ጥቅምት 29፣ 2006 ባደረገው ስብሰባ በሳዑዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ በሀገሪቱመንግስት የጸጥታ ሀይሎችእየደረሰ ያለውን ህገወጥ እስራት፣ድብደባና ስቃይ በታላቅ ሀዘንና አንክሮ እንዳጤነው ገል ል።
ሸንጎው ለዚህ ግፍ ሰለባዎችና ለቤተሰቦቻቸው የተሰማውን ሀዘን በመግለጽ ከጎናቸው እንደሚቆምምአረጋግጧል።
በተመሣሳይ የ ኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ( ኢህአፓ) ሳውዲ አረብያ በዜጎቻችን ላይ እያደረሰች ያለውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሁሉ መኮንንና ማውገዝ ቀነ ቀጠሮ የማይሰጠው ግዳጅ ነው ብሏል። የሳውዲ ወዳጅ የሆኑት ምዕራባውያንም የሚፈጸመውን ግፍ እንዲያወግዙ ጥሪ ያስፈልጋችዋል- ያለው ኢህአፓ፤ ከዚህ በተያያዘ የሚደረጉት ሰልፍፎችና ተቃውሞዎች ጸረ ሕዝቡን ወያኔን በዋና ተጠያቂነት የሚያጋልጥና የሚያወግዝ መሆን አለበት ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የባለ ራዕይ ወጣቶች ማህበር ባወጣው መግለጫ ለቀናት የተራዘመው በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው አረመኔያዊ ድርጊት የሰብአዊና የዴሞክራሲያዊ መብት እረገጣ ብቻ ሳይሆን በሀገር ሉአላዊነት ላይ የተቃጣ አደጋ በመሆኑ የኢትዮጵያ መንግስት ተጨባጭ የሆነ አስቸኳይ እርምጃ ሊወስድ ይገባል ብሏል።
በተለይም የዚህ አደጋ ተጎጂና ተጋላጭ የሆኑት የዚህች ደሃ አገራችን ተረካቢና አንቀሳቃሽ የሚባለው ወጣት ትውልድ በመሆኑ ይዋል ይደር ሳይባል መብታቸው ተከብሮ ባስቸኳይ ወደ እናት ሀገራቸው የሚመጡበት እና የሚመለሱበት መንገድ በአፋጣኝ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡መንግስት በህዝባችን ላይየደረሰውን ሰብዓዊም ሆነ ቁሳዊ ውድመት ተከታትሎ የ ጉዳዩ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እናስታውቃለን ያለው ማህበሩ መላው ኢትዮጵያውያን ድርጊቱን ለማውገዝ ና ለማስቆም የጀመሩትን ዓለማቀፍ እንቅስቃሴ አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርቧል።መንግስት በህዝባችን ላይ የደረሰውን ሰብዓዊም ሆነ ቁሳዊ ውድመት እና ጉድለት ተከታትሎ የጉዳዩ ባለቤት ለሆነው የኢትዮጵያ ህዝብ ይፋ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡በተለይም የዚህ አደጋ ተጎጂና ተጋላጭ የሆኑት የዚህች ደሃ አገራችን ተረካቢና አንቀሳቃሽ የሚባለው ወጣት ትውልድ በመሆኑ ይዋል ይደር ሳይባል መብታቸው ተከብሮ ባስቸኳይ ወደ እናት ሀገራቸው የሚመጡበት እና የሚመለሱበት መንገድ በአፋጣኝ ሊዘጋጅ ይገባልበተለይም የዚህ አደጋ ተጎጂና ተጋላጭ የሆኑት የዚህች ደሃ አገራችን ተረካቢና አንቀሳቃሽ የሚባለው ወጣት ትውልድ በመሆኑ ይዋል ይደር ሳይባል መብታቸው ተከብሮ ባስቸኳይ ወደ እናት ሀገራቸው የሚመጡበት እና የሚመለሱበት መንገድ በአፋጣኝ ሊዘጋጅ ይገባል፡፡