ኢሳት በባህል አምባሳደርነት የተካፈለበት የስዊዝ አፍሪካ የባህል ፌስቲቫል በተሳካ ሁኔታ ተካሄደ

ነሀሴ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በየአመቱ  በስዊዘርላንድ  የመንግስት  መቀመጫ  በሆነችው  በበርን  ከተማ  የሚካሄደው ታላቁ የስዊዝ አፍሪካ ፌስቲቫል ከመቸውም  ጊዜ  በደመቀ ሁኔታ ተጀምሮ ተጠናቋል

የኢትዮጵያ  ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት ከሚዲያ አውታርነት በተጨማሪ  በባህል  አምባሳደርነት በተካፈለበት :  በስዊዝ  የሚገኙ  ኢትዮጵያውያን  በተለያዩ  የብሄር  ብሄረሰቦችን  አልባሳት ተውበውና የቀስተ ደመና አምሳል በሆነው አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ አላማ አሸብርቀው የታዩበት የዘንድሮው ፌስቲቫል  ከኣፍሪካ ፌስቲቫልነትወደ ኢትዮጵያ ፌስቲቫልነትየተቀየረበት ይመስል ነበር።

በስዊዘርላንዷ በርን ከተማና  አካባቢዋ  የሚኖሩ  ኢትዮጵያውያን  ኢሳት  አገልግሎት  መስጠት ከጀመረበት  ጊዜ  ጀምረው  አጋርነታቸውንና  ድጋፋቸውን  ያላቋረጡ  ሲሆን  በዘንድሮው  ፌስቲቫል ላይ  ኢሳትን  በኣለማቀፍ   መደረክ  ላይ  ያለውን  የኢትዮጵያ  ህዝብ  የስሜት  ህዋስ  መሆኑን  ለማሳየት  ያደረጉት  ጥረትና  የተገኘው ውጤት  ከተጠበቀው  በላይ  የነበረና  በሌሎች  የዐለማችን ክፍሎች  ለሚገኙ  ኢትዮጵያውያን  በኣርኣያነት የሚታይ ሆኗል ።

« ሰው  እንጂ  ህዝብ  አላጣሽም » የሚለው  የወጣቱ  ደራሲ  ሄኖክ  የሺጥላ  አዲስ  መፅሃፍ  « የቃሊቲው መንግስት »  የሚለው  የደራሲና  ጋዜጠኛ  ሲሳይ  አጌና  መፅሃፍ  ለገበያ  ቀርበው  የተሸጡ  ሲሆን  በቅርቡ  የጤንነት  ችግር  ገጥሟቸው  ለነበሩት   ለቀድሞው የኢትያጵያ ፕሬዚደንትና  የአሁኑ  የተቃዋሚው  የአንድነት  ለዲሞክራሲና ለፍትህ  ፓርቲ  ሊቀመንበር  ለሆኑት  ለዶ/ር  ነጋሶ ጊዳዳ  መልካም  ምኞትን  ከመግለፅ  ባለፈ የገንዘብ  ድጋፍም  ተደርጎላቸዋል

በስዊዘርላንድ  የሚገኘው  የኢሳት ርዳታና ድጋፍ አስተባባሪ  አካልም  በተለያዩ  የስዊዝ  ከተሞች በሚካሄዱ  የተለያዩ  ብሄራዊ  አሕጉራዊና  አለም አቀፋዊ  ዝግጅቶች ላይ  ከሃገር  ወዳድ  ኢትዮጵያውያን  ጋር በመተባበር  በቀጣይነት የሚያካሂድ  መሆኑም በቦታው ላይ ተገልፆል::

____________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide