ነሃሴ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በባህርዳር ከተማ ተደርጎ በነበረው ስብሰባ ላይ የምክር ቤት አባላት ፣” የህዝብ ወኪሎች ብንሆንም ስራ አስፈጻሚው አካል የምናቀርበውን
ሪፖርት አይቀበልም” ብለዋል። አንድ ኢንቨስተር ከአንድ የህዝብ ተመራጭ የተሻለ ተሰሚነት አለው ያሉት ተማራጮች መፍትሄ ለማምጣት ካልቻልን የእኛ ተመራጭነት ምንድነው ሲሉ
የምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቅርበዋል የህዝብ ተወካዮቹ እንደገለጹት በአሁኑ ጊዜ በፍድር ቤቶች አካባቢ ከፍተኛ ችግር እንዳለም ገልጸዋል። አንድ ተወካይ የመንግስት ሆስፒታሎች
እየተዳከሙና መድሃኒቶች እየተሸጡ፣ ህዝቡም ከመንግስት የጤና ተቋማት ይልቅ ወደ ግል እየሄዱ መሆኑን ገልጸዋል።
ህብረተሰባችን ምን ላይ ነው ያለውን የማጥናት ችግር አለ ያሉት ሌላው ተወካይ፣ በምዞርባቸው ቦታዎች ሁሉ ህዝቡ መውደቂያ አጣን ብሎ እንደሚጮህ ተናግረዋል።
ኢህአዴግ ለመጪው ምርጫ ዝግጅት በሚመስል መልኩ በተለያዩ ደረጃ የሚገኙ የህዝብ ተወካይ የሚላቸውን ሰዎች እየጠራ በማወያየት ላይ ነው።እስካሁን ድረስ በተደረጉት ውይይቶች
አብዛኛው ተወያይ በአገሪቱ ውስጥ ከፍተኛ ሆነ የኢኮኖሚ ና የአስተዳደር ችግሮች እንዳሉ በድፍረት መግለጹን ኢሳት ሲዘግብ መቆየቱ ይተወቃል።