ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአፍሪካ ህብረት የተሰየመ በቀድሞ የናይጄረያ ፕሬዘዳንት ኦለሰንጎ ኦበሳጆ የሚመራ የልኡካን ቡድን ወደደቡብ ሱዳን ያመራ ሲሆን ስራውም በደቡብ ሱዳን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት መመርመርና ለአፍሪካ ህብረት አስፈላጊውን የመፍተሄ ሃሳብ ማቅረብ ይሆናል::
የልዑካን ቡድኑ ፕረዜዳንት ሳልቫኪርንና የተቃዋሚውን መሪ ሬክ ማቻርን እንደሚያነጋግር ሲታወቅ በጦርነቱም ስቃይ የደረሰባቸውን ሰዎች እንደሚያነጋግር ታውቋል::
ይህ በዚህ እያለ በዛሬው እለት ፕሬዝዳንት ሳልቫኬርና በተቃዋሚው መሪ በሬክ ማቻር መካከል ይካሄዳል የተባለው ድርድር ላልተወሰኔ ግዜ ተራዝሟል።
አንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ድርድሩን ከሚመሩት ሰዎች የብቃት ማነስ እየታየ መሆኑን በመናገር ላይ ናቸው። ድርድሩን በዋናነት የሚመሩት የቀድሞው የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን ናቸው።