ሐምሌ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የየመን መንግስት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ለመንግስት የጸጥታ ሃይሎች ህገወጥ በሆነ መልኩ አሳልፈው ከሰጡዋቸው በሁዋላ ኢትዮጵያውያን አሁንም ቁጣቸውን እየገለጹ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ” የአቶ አንዳርጋቸው መታሰር ልብን የሚሰብር ቢሆንም፣ ወሳኙ ነገር ማዘን ሳይሆን ለለውጥ ቆርጦ በመነሳት መታገል ነው” ብለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የየመን መንግስት የወሰደውን እርምጃ እንዲሁም የኢህአዴግ መንግስት አቶ አንዳርጋቸውን አስሮ ማሰቃየቱን በመቃወም የሚያደርጉትን ተቃውሞ እንደቀጠሉ ነው። በአሁኑ ወቅት የጸጥታ ችግር በሚታይባት እስራኤል የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቴላቪቭ ባደረጉት ተቃውሞ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተፈጸመውን ህገወጥ እርምጃ አውግዘዋል። ኢትዮጵያውያኑ እንግሊዝ በአቶ አንዳርጋቸው ጉዳይ ጣልቃ እንድትገባና የሚለቀቅበትን መንገድ እንድትፈልግም ጠይቀዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ መንግስት በሽብርተኝነት ሰበብ ያሰራቸውን በአገር ውስጥ በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉትን ፖለቲከኞች እንዲፈታ አንድነትና መኢአድ በጋራ እንዲሁም ሰማያዊ ፓርቲ ጠይቀዋል።አንድነት እና መኢአድ ” ኢህአዴግ በምርጫ ዋዜማ የጀመረው እስር በአምባገነንነት መስመሩ ለመቀጠል የቆረጠ መሆኑን የሚያረጋገጥ ነው” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ” የሰሞኑ እስር እንደተለመደው የተቀነባበረ የስርዓቱ ድራማ ከመሆኑም በተጨማሪየ2007ንሀገራቀፍምርጫበተለመደውማሸማቀቅናማወናበድለመውሰድየተጀመረየመጀመሪያርምጃነውብለንምእናምናለን” ብሎአል።
ፓርቲዎቹ ” የአንድነትና መኢአድ አባላትንና አመራሮቻችንን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በማሰቃየትና በማሸማቀቅ በመደብደብ የአካል ማጉደል ጉዳት በማድረስ የሚያደርገውን አስነዋሪ ተግባር አውግዘው፣ በግፍ የተታሰሩት አቶ ሀብታሙ አያሌው ፤ አቶ ዳንኤል ሺበሺ ፤ አቶ አብርሃ ደስታ እና አቶ የሺዋስ አሰፋ እንዲሁም በስርዓቱ በፖለቲካ አመለካከታቸውና እምነታቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ፖለቲከኞች ፤ ጋዜጠኞችና ብሎገሮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ” አሳስበዋል። ፓርቲዎቹ “በተቃውሞጎራየተሰለፉፓርቲዎችይህንህገወጥእስርበማውገዝእንዲሁምኢ-ፍትሀዊምርጫለማካሄድየሚደረገውንሩጫበመቃወምእጅለእጅተያይዘውእንዲቆሙ”ጠይቀው፣ ይህንንህገ-ወጥነት በህዝባዊና ሠላማዊ ንቅናቄ ፣ በነፃና ፍትሓዊ ምርጫ መለወጥ እንዲቻል በጋራ እንዲሰሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በበኩላቸው ገዢው ፓርቲ ስለምርጫ ሳይሆን አገርን ለማጥፋት እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ኢትዮጵያ የት ነው ያለችው ሲሉ የጠየቁት ኢ/ር ይልቃል፣ ያመጸው ሁሉ ሽብረተኛ ሆኗል፣ በሰላማዊ ትግል የሚታገለውም፣ ጋዜጠኛውም ሽብርተኛ ሆኗል ያሉት ኢ/ር ይልቃል፣ አገሩን ማስተዳደሩ ከአቅማቸው በላይ በመሆኑ፣ የትግሉ እንቅስቃሴ ከፍ ወዳለ ደረጃ መሸጋጋሩን ገልጸዋል።