የአቶ አስገደ ገብረስላሴ ልጅ ተፈረደበት

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የታዋቂው ፖለቲከኛ የአቶ አስገደ ልጅ አህፎም ስገደ ያለ በቂ ምክንያት በተለያዩ እስር ቤቶች እየተዘዋወረ ሲታሰር ከቆየ በሁዋላ ፍርድ ቤት በ4 አመት ከአምስት ወር እስራት እንዲታሰር ፍርዶበታል። አህፎም ፎርጅድ ሰርተፊኬት ሰርቷል ተብሎ ክስ የተመሰረተበት ሲሆን፣ አቃቢ ህግ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርብ ፍርድ ቤት ውሳኔ ማስተላለፉ ብዙዎችን አስገርሟል።

አቶ አስገደ ገብረስላሴ ህወሃት አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በሁዋላ ድርጅቱን መልቀቃቸው ይታወቃል። በህወሃት ላይ ጠንካራ ነቀፌታዎችን በመጽሃፍ ፣ በጋዜጦችና በተለያዩ የመገናናኛ ብዙሃን በማቅረብ የሚታወቁት አቶ አስገደ፣ ከዚህ ቀደም ሶስቱም ልጆቻቸው ታስረውባቸው ነበር።

የአሁኑ እርምጃ አቶ አስገደን ለመበቀል ተብሎ የተወሰደ እርምጃ መሆኑን ታዛቢዎች ይገልጻሉ።