ጥቅምት ፳፱ (ሀያ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ኢሳት ትናንት በሰበር ዜና እንዳቀረበው ሰራተኞቹ ተቃውሞውን ያነሱት ከስራው መጓተት፣ ከክፍያ ፣ ከስራ ከባቢ ከመጠለያና ተዛማች ችግሮች ጋር በተያያዘ ነው። ሳሊኒ ከግብጽ መንግስት ጋር የተመሳጠረ በሚመስል ሁኔታ ስራው እንዳይሰራ እያጓተተው ነው፣ ሰራተኛው አለስራ ጊዜውን እያባካነ ነው፣ የሚከፈለን ክፍያ ከስራው ጋር የተመጣጠጠነ አይደለም፣ የምግብ፣ የመጠለያና ሌሎችም ችግሮች አሉብን በማለት የስራ ማቆም አድማ ያደረጉት ሰራተኞች ፣ ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ሙከራ ቢያደርጉም አንድ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን በመንግስት ሰረተኞችን በማስፈራራታቸው ዛሬ ገሚሶቹ ያለፍላጎታቸው ስራ መጀመራቸው ታውቛል።
ማስፈራሪያውን የሰጡት ባለስልጣን ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ እንደሆኑ ለማወቅ የታቸለ ሲሆን፣ እርሳቸው ስፍራውን እንደለቀቁ ሰረተኞቹ ከየካምፓቸው እየተጠሩ በአናድ ስፍራ እንዲሰባሰቡ ከተደረጉ በሁዋላ በብርድና በምግብ እንዲቀጡ ተደርጋል።
አካባቢው በከፍተኛ የደህንነት ክትትል ስር የሚገኝ በመሆኑ ሰረተኞች እንደልባቸው ለመናገር ድፍረቱን አላገኙም። ይሁን እንጅ ኢሳት
በስፍራው ላይ የሚገኝን አንድን ባለሙያ አነጋግሮ እንደተረዳው የአባይ ግድብ ፍጻሜ እንደተባለው በ7 አመት ሊጠናቀቅ አይችልም
የአባይ ግድብ ያለምንም ጫረታ ስራውን በተቋረጠው በጣሊያኑ ሳሊኒ ኩባንያ የሚሰራ ነው። የአባይ ግድብ ፕሮጀክት የአረብ አብዮት በተነሳ ማግስት ይፋ ማደረጉ ይታወቃል። ፕሮጅክቱ ይፋ ከተደረገ በሁዋላ ሰራተኞች ና ባለሀብቶች ቦንድ እንዲገዙ ሲደረግ ቆይቷል።
በዚህ ዘገባ ዙሪያ የመንግስት ባለስልጣናትንም ሆነ የሳሊኒ ኩባንያ ባለስልጣናትን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።