(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 25/2011)የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት በከተማዋ በተፈጠረ ረብሻ ለሌላ ጊዜ ተራዘመ፡፡
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማህኝ አስረስ ሰብሰባውን በሀይል ለማደናቀፍ መሞከሩ ዲሞክራሲን ወደኋላ የሚመልስ ነው ብለዋል።
የአርበኞች ግንቦት 7 በባሕር ዳር ከተማ ክልል ምክር ቤት አዳራሽ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ከገጠመው ተቃውሞ ጋር ተያይዞ ወደ ሌላ ግዜ ተራዝሟል።
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡
ወጣቶች ‹‹ግንቦት ሰባት የአማራ ጠላት ነው›› በማለት ውይይት በተጠራበት አዳራሽ አካባቢ ተቃውሞ አሰምተዋል፡፡
ንቅናቄው ለአዳራሽ ውይይቱ ተሳታፊዎችን በማስታወቂያና በመግቢያ ወረቀት መጋበዙን የውይይት ኮሚቴው አባል አቶ ዓለሙ ፈጠነ ተናግረዋል፡፡
‹‹ነገር ግን ወጣቶች ወደ አዳራሽ በመግባት የሰቀልናቸውን ጽሑፎች አውርደውብናል፣ የራሳቸውን ጽሑፍ በመስቀልም አውከውናል›› ብለዋል አቶ ዓለሙ፡፡
የአማራ ክልል የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አሰማሀኝ አስረስ ሰብሰባውን በሀይል ለማደናቀፍ መሞከሩ ዲሞክራሲን ወደ ኋላ የሚመልስ ነው ብለዋል።
አንደ አቶ አሰማሀኝ ገለጻ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ ህጋዊ ፓርቲ በመሆኑ ከደጋፊዎቹ ጋር ሰብሰባ የማከሄድ መብት አለው።ነገር ግን የተወሰኑ ሰዎች ባነር በመቅደድ ወንበር በመስበር ያደረጉት እንቕስቃሴ ህገወጥ ነው ብለዋል። በተቃውሞው ተኩስ የሰማ እነደነበርና ያልታወቁ ታጣቂዎችም ነበሩ ብለዋል።
ተቃውሞ ያቀረቡት ወጣቶች በበኩላቸው ‹‹ግንቦት 7 የአማራን ብሔርተኝት የሚያዳክም፣ በኢትዮጵያዊነት ስም አማራን እንዳይደራጅ የሚያሴር፣ ሀገሪቱ በብሔር ፖለቲካ መወጠሯን እያወቀ አማራ ብቻ ስለኢትዮጵያ እንዲያቀነቅን የሚወተውት ፀረ-አማራ ንቅናቄ ነው›› ብለዋል፡፡
ንቅናቄው ለሚፈልጋቸው ግለሰቦች ብቻ ወደ ስብሰባው መግቢያ ወረቀት አዘጋጅቶ ህዝብ ላወያይ ብሎ ማሰብ ተገቢነት የለውም ነው ያሉት ወጣቶቹ።ከዚህ ጋር በተያያዘም የአርበኞች ግንቦት ሰባት ደጋፊዎች የተቃዋሚዎችን ድርጊት በማወገዝ ለሰልፍ ቢወጡም የንቅናቄው ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ስብሰባው ሊላ ጊዜ እንደሚካሄድ በማሳወቅ ለሰላም ሲባል እንዲረጋጉ በማድረግ ወደ መጡበት እንዲመለሱ አድረገዋል ተብሏል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ባስተላለፉት መልዕክት ተፎካካሪ ፖርቲዎች የተስማሙበትን የጋራ የቃል ኪዳን ሰነድ መሰረት በማድረግ ቀጣይ ስራዎችን አንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ንቅናቄው በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታዎች እና ከህዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች መልስ ለመስጠት ከባህርዳር ከተማ ነዋሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ለመምከር አስቦ እንደነበር የባህርዳር ከተማ የአርበኞች ግንቦት 7 ፀሀፊ አቶ መንግስቱ አማረ ለአማራ መገናኛ ብዙሀን ተናግረዋል ።