የአሜሪካ መንግስት በእነ እስክንድር ነጋ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወገዘ በአስቸኳይ እንዲፈቱም ጠየቀ

ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የስቴት ዲፓርትመንት ቃል አቀባይ የሆኑት ቪክቶሪያ ኑላንድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የአሜሪካ መንግስት በአጠቃላዩ የፍርድ ሂደትናና ውሳኔ ላይ አለመደሰቱን ገልጠዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የጸረ ሽብርተኝነት ህጉን በነፃ ሀሳባቸውን የሚገልጡ  ጋዜጠኞችን እና የተቃዋሚ የፓለቲካ ድርጅት መሪዎችን ለማሰር እየተጠቀመበት ነው ሲሉም ወቅሰዋል።

ውሳኔው ኢትዮጵያውያን በህገመንግስቱ የተቀመጠላቸውን መብቶች ለመጠቀም ችግር እየገጠማቸው መምጣቱን ያሳያል ያሉት የስቴት ዲፓርትመንት ባለስልጣን፣ የኢትዮጵያ መንግስት የዜጎችን ሀሳብን በነጻነት የመግለጥ መብትን ማፈኑን እንዲያቆም እንዲሁም መሰረታዊ የሆነውን ሰብአዊ መብታቸውን በመጠቀማቸው የታሰሩትን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቀዋል።

በተመሳሳይ ዜናም በስዊድን የሚገኙ አትዮጵያን በእነ አቶ አንዱአለም አራጌ ላይ የተላለፈውን ውሳኔ አወግዘዋል።

ኢትዮጵያውያኑ ትናንት ባካሂዱት የተቃውሞ ሰልፍ፣ የመልስ መንግስት ህግን ከለላ በማድረግ በፖለቲካ መሪዎች፣ በጋዜጠኞችና እና በሲቪክ መሪዎች ላይ ያስተላለፈውን ውሳኔ ተቃውመዋል።

ሰልፈኞቹ የፖለቲካ እስረኞች በሙሉ እንዲፈቱ ጥያቄ አቅርበዋል።በኢትዮጵያ ኢምባሲ ፊትለፊት በተደረገው ተቃውሞ ኢትዮጵያውያኑ የመለስን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮችን አስምተዋል።

የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ሶስተኛ ወንጀል በእስር ላይ ቢመገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር አባላት በሆኑት በአቶ አንዱአለም አራጌና አቶ ናትናኤል መኮንን፣ በቅደም ተከትል ፣ እድሜ ልክና 18 አመት እንዲሁም በአቶ ክንፈሚካኤል በረደድ ላይ የ25 አመት ጽኑ እስራት መፍረዱ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide