አቶ መለስ ዜናዊ በጸና መታመማቸው ተዘገበ

ሐምሌ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-አቶ መለስ ዜናዊ የጤንነት ሁኔታ አስጊ ደረጃ ላይ በመድረሱ ረቡእ እለት ብራሰልስ በሚገኘው ሴት ሉክ ሆስፒታል ተመልሰው መተኛታቸውን የግንቦት7 ራዲዮ ዘግቧል።

አቶ መለስ በህይወት የሚቆዩበት ጊዜ ቀናት ወይም ወራት ሊሆኑ ይችላሉ የሚለው ዘገባ፣ አቶ መለስ በካንሰር በሽታ እየተሰቃዩ መሆኑንም ጠቁሟል ። የኢትዮጵያ መንግስት በአቶ መለስ ህመም ዙሪያ እስካሁን የሰጠው መግለጫ የለም።  ይሁን እንጅ እርሳቸው የሚገኙበት አንድ የሽልማት ስነስርአት እንዲሰረዝ መደረጉ ይታወቃል። ፓርላማውም ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ ያለ አቶ መለስ ዜናዊ ተሳትፎ እንዲዘጋ መደረጉም ይታወሳል።

አቶ መለስ በነገው እለት የሚጀመረውን የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በንግግር ከሚከፍቱት መካከል አንዱ ናቸው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide