የአሜሪካው ፕሬዚዳንት በለንደን ከፍተኛ ተቃውሞ ገጠማቸው
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 6 ቀን 2010 ዓ/ም ) እንግሊዝን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ፕ/ት ዶናልድ ትራምፕ የህጻን ምስላቸውን ከፍ አድርገው በያዙ ተቃዋሚዎች ሲወገዙ ውለዋል። አብዛኞቹ ሰልፈኞች ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞችን በተመለከተ የሚከተሉትን ፖሊሲዎች አውግዘዋል።
እንግሊዝ ከአውሮፓ ህብረት ጋር ያላትን ህብረት ማቋረጡዋን በተመለከተ ፕሬዚዳንቱ በአንድ ቀን ልዩነት እርስ በርስ የሚጣረስ ንግግር መናገራቸው የመገናኛ ብዙሃን የትኩረት አቅጣጫ ሆኗል።
ፕሬዚዳንት ትራምፕ ከእንግሊዟን ንግስት ጋር በዊንድሶር ቤተመንግስት ይገናኛሉ።ወደ ፊንላንድ በማቅናትም በሄልስንኪ የሩሲያውን መሪ ቭላድሜር ፑቲንን ያገኛሉ።