የአማራ ክልል ኢንቨስትመንት በማስፈጸም ረገድ በርካታ ፈተናዎች እንዳጋጠሙት ተገለጸ፡፡
(ኢሳት ዜና ግንቦት 13 ቀን 2010 ዓ/ም) የማስፈጸም ችግሩ በአንድ ሴክተር መስሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን በሁሉም ሴክተሮቻችን የሚታይ ችግር ነው የሚሉት
የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣን አብዛኛውን ነገር እያሰረ ያለው የማስፈጸሙ ችግር እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ ከኢንቨስትመንት አኳያ ባለሃብት መማምጣት ላይ ችግር እንደሌለ ሚገልጹት ከፍተኛ አመራር ዋናው ችግር የመጡትን
ባለሃብቶች በመጡበት ፍጥነት ወደ ስራ ያለማስገባት መሰረታዊ ችግር እንደሆነ ይገልጻሉ፡፡ በዚህ ዓመት በማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለመሰማራት የጠየቁ ከሁለት ሽህ በላይ ባለ ሃብቶች ቢኖርም
፣ከነዚህ ውስጥ ወደ ስራ የገቡት 591 ብቻ ናቸው።ባለሃብቱ እንደመጣ መሬት በማግኘት ወደ ስራ የሚገባበትን አሰራር የክልሉ መንግስት በግልጽ ማስቀመጡን የሚጠቅሱት ከፍተኛ አመራር ፍላጎቱንና የመሬቱን አቅርቦት አመጠጣጥኖ በመስራት በኩል መሰረታዊ ችግሮች በአመራሩ በኩል እንደሚስተዋሉ ተናግረዋል፡፡
“ባለሃብቱ በክልሉ ላይ ያሉ ዕድሎችን በአመዛኙ አውቋቸዋል” የሚሉት ከፍተኛ አመራር ዋና ችግር ሆኖ የሚታየው በዚህ ክልል ላይ ማልማት አለብን ብለው የሚመጡትን ባለሃብቶች ከማስተናገድ ጋር ያለ ችግር መሆኑን አብራርተዋል፡፡”የተመዘገበው ባለሃብት ሳስተናገድ ሌላ ባለሃብት መሳብ ለምን ያስፈልጋል ?” የሚል አመለካከት ማራመዳቸውን የሚገልጹት
ባለሰልጣን ፣በሁለተኛነት የሚያነሱት በበላይ አመራሮች በስፋት የሚታየው የአቅም ችግር መኖር የክልሉን ኢንቨስትመንት በተፈለገው ፍጥነት ለማራመድ እንቅፋት መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡