(ኢሳት ዜና –ነሐሴ 19/2009)የአማራና የቅማንት ህዝብ በማለት በአንድ ላይ የሚኖርን ሕብረተሰብ ለመከፋፈል እየተደረገ ያለው ሴራ መጨረሻው ጥፋት ሊሆን እንደሚችል የአካባቢው ተወላጅ የሆኑ ሁለት ኢትዮጵያውያን አመለከቱ።
የቅማንት ተወላጅና የጎንደር ሕብረት ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ንጋቱና የአገው ምድር ተወላጅ የሆኑት አቶ አይሸሽም ሰለሞን እንደገለጹት በሕወሃት /ኢሃአዴግ የሚመራው አገዛዝ ሕዝብን በመከፋፈል ሐገሪቱን ይበልጥ ወደማያባራ ግጭት በመውሰድ የጥፋት እርምጃ እየፈጸመ ነው።
የቅማንትና የአማራ ሕዝብን ለመከፋፈል የተፈለገውም የትግራይ የግዛት መስፋፋት ሕልምን እውን ለማድረግ በሕወሃት ጉዳይ አስፈጻሚዎች ለብአዴን የቤት ስራ በመስጠቱ ነው ብለዋል።
በሰሜን ጎንደር የቅማንትን ህዝብ ለብቻው ለመከለል በሚል የአካባቢውን ካድሬዎች በማሰማራት ቅስቀሳና ዘመቻ ሲካሄድ ቆይቷል።
ይህ በሆነበት ጊዜ ግን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በመጀመሪያ በነበራቸው አቋም የቅማንት ሕዝብ በምንም መልኩ ከአማራው ሕዝብ የሚነጠል እንዳልሆነ አጽንኦት በመስጠት የሕወሃትን ስራና ስውር ደባ አውቀውም ይሁን ሳያውቁ ለመቃወም ሞክረው ነበር።
ይህም ሆኖ ግን የአማራ ክልል መስተዳድር ፕሬዝዳንት በአቋማቸው ሳይጸኑ የቅማንት ሕዝብ የራሱ ዞን ይኑረው በሚል በ126 ቀበሌዎች ላይ ጥያቄ ቀርቦ የመለየት ስራው በዘመቻ መልክ ቀጥሏል።
በኋላም የአካባቢው ህዝብ ሰጥቷል በተባለው ድምጽ ከአማራነት ይልቅ ቅማንት ነን አሉ የተባሉ 42 ቀበሌዎች መለየታቸው ነው የተገለጸው።
አሁን ደግሞ ማንነታቸው ተቀላቅሏል የተባሉ 12 ቀበሌዎች ነዋሪዎች በሕዝበ ውሳኔ ስም በምርጫ ቦርድ አማካኝነት በመጭው መስከረም መጨረሻ ድምጽ ይሰጣሉ ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።
የዚህ ጉዳይ አላማው ህዝብን በመከፋፈል ጥፋት ለማድረስ እንጂ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዳልሆነ የቅማንት ተወላጅና የጎንደር ሕብረት ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ንጋቱ ለኢሳት ተናግረዋል።
በተመሳሳይ መልኩ በአገው ምድር ከአማራው ተነጥሎ የአዊ ዞን በሚል የተከፈለው ዞን አካባቢ ተወላጅ አቶ አይሸሽም ሰለሞን በበኩላቸው ሕዝብን ለብቻ መከለል ለዘረፋ እንዲያመች እንጂ ለልማት ተጠቃሚነት አይደለም ብለዋል።
በሰሜን ጎንደር ያሉ ቅማንቶችም ሆነ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ የአገው ተወላጆችን በመከፋፈል አሁን ያለው አገዛዝ ሕዝብን እየነጣጠለ ያለው የትግራይን ግዛት ለማስፋፋት ሕወሃት ካለው ፍላጎት እንደሚመነጭም ሁለቱም የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል። – አቶ አበበ ንጋቱና አቶ አይሸሽም ሰለሞን።
የትግራይ ክልል ሆን ተብሎ ከሱዳን ጋር እንዲዋሰን የተደረገበትና ከቤንሻንጉል፣ ጋምቤላና አማራ ክልል መሬት ቆርሶ የተዘጋጀው ካርታ በብዙዎች ዘንድ ሴራው ተጋልጦ ሕዝብ እንዲያውቀው ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን ይህንኑ የትግራይን የመስፋፋት ህልም የያዘውን ካርታ በዜና እወጃ ሰአቱ ሰሞኑን በድንገት ማሳየቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።
ወላጅና የጎንደር ሕብረት ስራ አስፈጻሚ አቶ አበበ ንጋቱና የአገው ምድር ተወላጅ የሆኑት አቶ አይሸሽም ሰለሞን እንደገለጹት በሕወሃት /ኢሃአዴግ የሚመራው አገዛዝ ሕዝብን መበከፋፈል ሐገሪቱን ይበልጥ ወደማያባራ ግጭት በመውሰድ የጥፋት እርምጃ እየፈጸመ ነው።
የቅማንትና የአማራ ሕዝብን ለመከፋፈል የተፈለገውም የትግራይ የግዛት መስፋፋት ሕልምን እውን ለማድረግ በሕወሃት ጉዳይ አስፈጻሚዎች የቤት ስራ በመስጠቱ ነው ብለዋል።
በሰሜን ጎንደር የቅማንትን ህዝብ ለብቻው ለመከለል በሚል የአካባቢውን ካድሬዎች በማሰማራት ቅስቀሳና ዘመቻ ሲካሄድ ቆይቷል።
ይህ በሆነበት ጊዜ ግን የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር በመጀመሪያ በነበራቸው አቋም የቅማንት ሕዝብ በምንም መልኩ ከአማራው ሕዝብ የሚነጠል እንዳልሆነ አጽናኦት በመስጠት የሕወሃትን ስራና ስውር ደባ ለመቃወም ሞክረው ነበር።
ይህም ሆኖ ግን በአቋማቸው ሳይጸኑ የቅማንት ሕዝብ የራሱ ዞን ይኑረው በሚል በ126 ቀበሌዎች ላይ ጥያቄ ቀርቦ የመለየት ስራው በዘመቻ መልክ ቀጥሏል።
በኋላም ህዝብ ሰጥቷል በተባለው ድምጽ ከአማራነት ይልቅ ቅማንት ነን አሉ የተባሉ 42 ቀበሌዎች መለየታቸው ነው የሚታወቀው።
አሁን ደግሞ ማንነታቸው ተቀላቅሏል የተባሉ 12 ቀበሌዎች በሕዝበ ውሳኔ ስም በምርጫ ቦርድ አማካኝነት በመጭው መስከረም መጨረሻ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ እየተጠበቀ ይገኛል።
በዚህ ጉዳይ ላይ አላማው ህዝብን በመከፋፈል ጥፋት ለማድረስ እንጂ ሕብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ እንዳልሆነ የቅማንት ተወላጅና የጎንደር ሕብረት ስራ አስፈጻሚ ለኢሳት ተናግረዋል።
በአገው ምድር በተመሳሳይ መልኩ ከአማራው ተነጥሎ የአዊ ዞን በሚል የተከፈለው አካባቢ ተወላጅ አቶ አይሸሽም በበኩላቸው ሕዝብን ለብቻ መከልለ ለዘረፋ እንዲያመች እንጂ ለልማት ተጠቃሚነት አይደለም ብለዋል።
በሰሜን ጎንደር ቅማንትም ሆነ በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚገኙ የአገው ተወላጆችን በመከፋፈል አሁን ያለው አገዛዝ ሕዝብን እየነጣጠለ ያለው የትግራይን ግዛት ለማስፋፋት ሕወሃት ካለው ፍላጎት እንደሚመነጭም ሁለቱም የአካባቢው ተወላጆች ለኢሳት ገልጸዋል።አቶ አበበ ንጋቱና አቶ አይሸሽም ሰለሞን።
የትግራይ ክልል ሆን ተብሎ ከሱዳን ጋር እንዲዋሰን የተደረገበትና ከቤንሻንጉል፣ ጋምቤላና አማራ ክልል መሬት ቆርሶ የተዘጋጀው ካርታ በብዙዎች ዘንድ ሴራው ተጋልጦ ሕዝብ እንዲያውቅ ተደርጓል።
የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን ይህንኑ የትግራይ የመስፋፋትን ህልም የያዘውን ካርታ በዜና እወጃ ሰአቱ በድንገት ማሳየቱ ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል።