ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንቱ በህዝቤ ላይ የኬሚካል የጦር መሳሪያ የምጠቀምበት ምንም ምክንያት ለም በማለት ለአንድ የአሜሪካ የቴሌቪዥን ጣቢያ ተናግረዋል።
አሜሪካ ሶሪያን ብትደበድብ አንዳንድ ደጋፊ አገሮች አጸፋዊ መልስ ለመስጠት መዘጋጀታቸውንም አላሳድ አክለው ገልጸዋል። ይሁን እንጅ እነዚህን አገሮች በስም ከመግለጽ ተቆጥበዋል።
አለም በሶሪያ ላይ ስለሚወደው የሀይል እርምጃ ተከፋፍሎአል። ፕሬዚዳንት ኦባማ በሶሪያ ላይ እርምጃ ካልተወሰደ ሌሎች አምባገነን መንግስታት ህዝባቸውን በተመሳሳይ መንገድ ከመግደል አይመለሱም በማለት ይከራከራሉ።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ፣ ጉዳዩን የሚያጣራው የድርጅቱ ልኡክ ሪፖርቱን እሰከሚያቀርብ ድረስ አሜሪካ እርምጃ ከመውሰድ እንድትቆጠብ ጠይቀዋል። ፈረንሳይን ጨምሮ ሌሎች የአውሮፓ አገራትም ይህን አቋም ደግፈዋል።