ታህሳስ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዋና አቃቢ ህጓ ምርመራውን ለማቋረጥ የተገደዱት ሁለቱ ዋና ምስክሮችን ለማግኘት ባለመቻላቸው ነው።
ፕሬዚዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ከ6 አመት በፊት በተነሳውና ከ1 ሺ 200 በላይ ሰዎች የተገደሉበትን የምርጫ ማግስት ረብሻ አነሳስተዋል በሚል ነው።
በምክትላቸው ዊሊያም ሩቶ ላይ የተጀመረው ክስ ይቀጠል አይቀጥል የታወቀ ነገር የለም። የአፍሪካ መሪዎች ክሱ እንዲቋረጥ ሲወተውቱ ቆይተዋል። ፕሬዚዳንቱ ክሱን እየተከታተሉ አገሪቱን ለመምራት አይችሉም በሚል ምክንያት ነው የአፍሪካ ህብረት ክሱ እንዲቋረጥ ውሳኔ ያሳለፈው። ክሱ እንዲቋረጥ ሲወተውቱ ከነበሩ አገሮች መካከል ኢትዮጵያ አንዳ ናት።
የጸጥታው ምክር ቤት የአፍሪካ መሪዎችን ጥያቄ ባለመቀበል ምርመራው እንዲቀጥል ወስኖ ነበር። አቃቢ ህጓ በፕሬዚዳንት ኡሁሩ ላይ የተጀመረው ክስ በማንኛውም ጊዜ ሊንቀሳቀስ እንደሚችል ተናግረዋል።