የቻግኒ ከተማ ነዋሪዎች 700 ሜትር ያለው ሰንደቃላማ በመያዝ ለዶ/ር አብይ አህመድ ድጋፋቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዜና ሰኔ 29 ቀን 2010 ዓ/ም) የከተማዋ ነዋሪዎች በባህርዳር ከተማ ተይዞ የተወጣውን ባንዲራ የሚበልጥ ረጅም ባንዲራ በመያዝ ዶ/ር አብይ አህመድ እያደረጉ ላሉት የለውጥ እንቅስቃሴ ድጋፉን ገልጿል።
የመተከል ከተማ ነዋሪዎች ፣ በአውራጃቸው የሚፈናቀሉና የሚገደሉ ወገኖች ሰቆቃ ይቁም፣ አገር በጭንቅላት እንጅ በአፈሙዝ አይገዛም የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎች በመያዝ ወደ አደባባይ ወጥተዋል።
በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በሚካሄዱ የድጋፍ ሰልፎች ላይ ኢትዮጵያውያን አርማ የሌለውን ባንዲራ በነጻነት ሲያውለበልቡ ይታያል። ኢህአዴግ ኮከብ የሌለው ባንዲራ ጥቅም ላይ እንዳይውል ህግ ደንግጎ እንደነበር ይታወቃል።