ሚያዚያ ፲፬ (አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሰብአዊ እርዳታ ተጠሪ ቶቢ ላንዘር: በደቡብ ሱዳን የተካሄደው ዘግናኝ ግድያ በጣም እንዳሳዘናቸው በመግለጽ ድርጊቱን የፈጸሙት ሰዎች ባስቸኳይ ለፍርድ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል::
ቶቢይ ላንዘር አንዳንድ ግለሰቦች የራዲዮ ጣብያን በመጠቀም ላደረጉት የጥላቻ ቅስቀሳ ተጠያቂ መሆናቸውንም ተናግረዋል።
ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በመጪው የፈረንጆች አዲስ አመት ከዚህ የበለጠ አሰቃቂ አደጋ ሊያጋጥም እንደሚችል ስጋታቸውን ገልጸዋል::
ይህ በዚህ እያለ የዑጋንዳ መከላከያ ሃይል ቦር የሚገኘውን የተባበሩት መንግስታት ጽህፈት ቤት ከአምስት ሺህ በላይ የሚገኙትን ስደተኞች ከሚሊሻዎች ጥቃት ለመከላከል ከመንግስታቱ የሰላም አስከባረ ሃይል መረከቡን አስታውቋል:።