የተማሪ ወላጆች ስለ ምርጫ ትምህርት እንዲወስዱ ታዘዙ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ  ትምህርት ቢሮ ባሰራጨው የጥሪ ወረቀት የተማሪዎች ወላጆች ስለክልሉ ሁኔታና ስለምርጫ

እንዲሁም ልጆቻቸው ስላለባቸው ሃላፊነት ስልጠና እንዲወስዱ ያዛል። ስልጠናው እንዳበቃም ወላጆች ስርተፊኬት ይቀበላሉ። ስልጠናው ከትናንት ጀምሮ በመሰጠት ላይ መሆኑንም ወኪላችን ገልጿል።