የበርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ የሳውል ፍሬዎች የሚል ፊልም አስመረቀ

መጋቢት ፳፩(ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአገራችን ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ ጋር በተያያዘ በርገን የኢሳት የድጋፍ ኮሚቴ አማካኝነት የተሰራው የሳውል ፍሬዎች በፈረንጆች አቆጣጠር ማርች 28 በበርገን ኖርዌይ ከተማ ተመርቋል።

በአይንሸት ገበያው  ተደርሶ በጋዜጠኛ ገሊላ መኮንን አርታኢነትና አዘጋጅነት በተሰራው ፊልም ፣ በበርገን እና አካባቢዋ የሚኖሩ 11 ኢትዮጵያውያን ተሳትፈውበታል።

በበርገን በተካሄደው ዝግጅት ለተሳታፊዎች የምሰክር ወረቀትና አበባ ተበርክቶላቸዋል። ፊልሙ በቅርቡ በተለያዩ ከተሞች መታየት የጀምራል።