ኢሳት ዜና:-የ 1997 ምርጫን ተከትሎ ከቅንጅት መሪዎችና ከሌሎች ጋዜጠኞች ጋር ታስሮ የነበረውና ዕድሜ ልክ ከተፈረደበት በሁዋላ በይቅርታ የተፈታው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ፣ ሰሞኑን ለስደት የተዳረገው መንግስት፤ የሰጠውን “ይቅርታ” በማንሳት ዳግም ወደ እስር ቤት ሊያስገባው መወሰኑን በመስማቱ መሆኑን ከኢሳት ጋር ባደረገው አጭር ቃለምልልስ ገልጧል
ጋዜጠኛ ዳዊት ፣እነ ውብሸት ታዬ፣ እስክንድ ነጋና ርእዮት አለሙ በሽብረተኝነት ተከሰው ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ስራቸውን በስጋት ያከናውኑ እንደነበር ተናገራል።
በቅርቡ የፍትህ አምደኛ የሆነው ታዋቂው ሀያሲ አቤ ቶክቾው ወይም አበበ ቶላ ፣ ከደህንነት ሀይሎች የተሰነዘረበትን ማስፈራሪያ ተከትሎ ከአገር መውጣቱ ይታወሳል።
የመለስ መንግስት ጠንካራ ሂስ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞችን አሸባሪ እያለ ወደ እስር ቤት ማጎሩን በማስመልከት አለማቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተንከባካቢ ድርጅት ማውገዙ ይታወሳል።