የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት መስክር የማሰማት ሂደት ቀጥሎአል

ግንቦት ፰ (ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከድምችን  ይሰማ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፤በረቡእ ጠዋቱችሎትለሙስሊም መሪዎቹለመመስከርበቦታውየተገኙትየአወሊያዩኒትመሪ -መምህርሙሐመድዑስማን- የችግሩ ፈጣሪ ነው ያሉት መጅሊስ-በአወሊያላይየፈጸመውንደባበዝርዝርአስረድተዋል፡፡

የመስጂድኢማሙእናየአወሊያአስተማሪዎችበመጅሊሱበመባረራቸውየተፈጠረውንቀውስለማረጋጋትከመጅሊሱአባላትጋርባደረጉትስብሰባየመጅሊሱዋናጸሀፊአቶአልሙሀመድሲራጅ፦ ‹‹ያመጣንላችሁዘመናዊሃይማኖትነው›› ሲሉመናገራቸውን  የመሰከሩት መምህር መሀመድ ኡስማን፤እናበታህሳስ 21- 2004 በተደረገሌላስብሰባየመጅሊሱየጸጥታጉዳዮችሐላፊ ‹‹በፊርማዬያባረርኳቸውንአስተማሪዎችበፊርማዬእመልሳቸዋለሁ›› በማለትስህተቱንማመኑንምተናግረዋል፡፡

በእለቱየስብሰባውንመድረክሲመራየነበረውየተማሪዎችካውንስልየማህበራዊናውጭግንኙነትሃላፊየነበረውተከሳሽሙባረክአደምእንደነበረ እና  ስብሰባውን  በሰላማዊመልኩእንደመራምገልጸዋል፡፡

ተማሪዎችተቃውሞባሰሙበትወቅትአቶአልሙሀመድሲራጅተማሪዎችላይማፌዛቸውንናከመጅሊስየመጡትየአወሊያአዲስዘበኛምአንድንተማሪበጥፊመምታታቸውን ተከትሎግርግርሲፈጠርም-ተማሪሙባረክአደምተማሪዎችንእንዳረጋጋ እንዲሁምየመጅሊሱንመኪናጎማያተነፈሱተማሪዎችንም- ‹‹መኪናውየሙስሊሙንብረትስለሆነአትንኩ›› በማለትየመጅሊሱጸሀፊበሰላምከግቢውወጥተውእንዲሄዱእንዳደረገ  መስክረዋል፡፡

ቀጥሎ በተደረገውይይት  ከተለያዩየመንግስትሃላፊዎችየተውጣጡሰዎችየተሰባሰቡበትቦርድበመጅሊሱምክትልፕሬዝዳንትአቶአዛምየበላይነትእንዲመራናየትምህርትቤቱካሪኩለምምእንደታቀደውእንዲለወጥመወሰኑንያስረዱት ምስክሩ፤ ይህን ተከትሎምተማሪዎች-“የተባረሩትኢማም፣የአስተዳደርሰዎች፣መምህራንናየጥበቃሰዎችእንዲመለሱመጠየቃቸውን እና አያይስውም ‹‹መጅሊስአይወክለንም›› የሚልጥያቄማንሳታቸውንጠቅሰዋል፡፡

ተከሳሽ ሙባረክ አደም በስብሰባው ወቅት ከመጅሊሱ ጸሀፊ አቶ አልሙሀመድሲራጅ እጅ ማይክራፎን መቀማት አለመቀማቱን የተጠየቁት መምህር መሀመድ ኡስማን፤ይህንንበፍጹምእንዳላደረገ መስክረዋል።
በረቡእ የከሰዓቱ ችሎት የአወሊያ ተማሪዎች መማክርት (ካውንስል) ፕሬዝዳንት ወጣት መለኩት አብዱልጀባር ምስክርነቱን ያሰማ ሲሆን በካውንስሉ ውስጥ እሱና ተከሳሽ ሙባረክ አደም የነበራቸውን ሀላፊነት አብራርቷል፡፡

በውስጥ ስለ ነበረው አስተዳደራዊ ችግር የመጅሊሱን ፕሬዝዳንት ተሰባስበው ባናገሩበት ወቅት ፕሬዝዳንቱ አቶ አህመዲን አብዱላሂ በዓረብኛ ቋንቋ  ‹‹አወሊያን ስሙን ሳይቀር መለወጥ እንፈልጋለን ››  ብለው መናገራቸውን  የመስከረው ወጣት መለኩት፤ በሲህም ምላሻቸው አስተዳደሩ-አወሊያን የመቀየር ፍላጎት እንዳለው መረዳቱን ተናግራል።

አክሎም  የአወሊያው ኢማም ሸኽ ዑመር ወሌ የተባረሩት መጅሊሱ ከሚያራምደው የአህባሽ አቋም ጋር የማይጣጣሙ በመሆናቸው መሆኑ እንደ ተነገራቸው በማውሳት ፤ በስብሰባ ላይ ጸሀፊው አቶ አልሙሀመድ ሲራጅ ‹‹እናንተ እምነታችሁን አታውቁም ፤እኛ ያመጣንላችሁሞ ደርን የሆነ እስልምና ነው››  ብሎ በግልጽ እስከ መናገር መድረሱን ጠቅሷል፡፡

መጅሊሱ ከአስተማሪዎች መባረር አስቀድሞ የዐረብኛ ተማሪዎችን ማባረሩን ፣ ታህሳስ 23/4004 አስተማሪዎቹ ሲባረሩ ተማሪዎች አንማርም የሚል ተቃውሞ መጀመራቸው ፣በታህሳስ 26 ምስድስት ጥያቄዎችን ያካተተ ደብዳቤ ለመጅሊስ ማስገባታቸውን እና በመቀጠልም አቶ አልሙሀመድ ሲራጅ ተማሪዎች ላይ በመሳለቃቸው  ‹‹መጅሊስ አይወክለንም ››  የሚል ጥያቄ መነሳቱን  ወጣት  መለኩት ለችሎቱ  አሰረድቱዋል።
ነገሮችበዚህመልኩከሄዱበኋላጥር 4 በዋለውየጁሙዓሰላትህዝብበተሰበሰበበትየተማሪዎቹንጥያቄለህዝብያቀረበውሙባረክአደምእስካሁንየነበረውንሰላማዊአካሄድእስከመጨረሻውመቀጠልእንዳለባቸውአጽንኦትሰጥቶመናገሩንያወሳው ምስክሩ፤ጉዳዩንህዝቡከተረከበናመልስይዞየሚመጣ 9 ኮሚቴካዋቀረበኋላየታሰሩተማሪዎችእንዲፈቱከፖሊስሃላፊዎችጋርበመነጋገርተማሪዎችበሰላምመበተናቸውንአስረድቷል፡፡

በችሎቱ ለወጣት መለኩት የመስቀለኛ ጥያቄዎች እንዲቀርቡለት ታስቦ የነበረ ቢሆንም ፤ዳኞች ‹‹የጤና ችግር አለብን ፤ከረፈደም መንገድ ይዘጋብናል ›› የሚል ምክንያት በመስጠታቸው ለሚቀጥለው  ቀን  ሐሙስ ካቆመበት እንዲቀጥል ተወስኖ  የእለቱ  ውሎ ተጠናቅቁዋል።

ትናንት ሐሙስ ግንቦት 7 ቀን የተሰየመው ችሎትም በረቡእ ውሎ  በሰዓት እጥረት ተቋርጦ የነበረውን የወጣት መለኩት አብዱል ጀባር የምስክርነት ቃል የመስቀለኛ ጥያቄ ሂደት አዳምጧል፡፡
‹‹አወሊያ የአክራሪዎች መፈልፈያ ነው ተብሏል ያልከው ከምን ተነስተህ ነው?›› የሚል ጥያቄ የቀረበለት ወጣት መለኩት፤ አባባሉን ከሰለፊያ ጋዜጣ ላይ እንዳነበበ በመናገር ምላሽ ሰጥቱዋል።ተማሪውንሲያስተባብርናለተቃውሞሲያነሳሳየነበረውተከሳሽሙባረክአደምመሆኑንአስመልክቶለቀረበለትጥያቄም ‹‹እሱአይደለም፤ይልቁንምየሁሉምተማሪአቋምነው›› ሲልተናግሯል፡፡

‹‹ከዘጠኙ ተመራጮች ውስጥ ያልተካተተ ሆኖ ሳለ ሙባረክ ለምን ነበር አወሊያ ላይ ከመንግስት ጋር በመወያየት የመጣውን ሪፖርት ያቀረበው?›› በሚል ለቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄም ፤ሙባረክሪፖርትያላቀረበመሆኑን- ማለትም  ሪፖርቱ በኮሚቴው አባል ማህሙድ ከመቅረቡ በፊት የተማሪውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ ሙባረክ ጥቅል ገለጻ ብቻ መስጠቱን አስረድቷል፡፡
‹‹ስለአህባሽስልጠናያወቅኩትበስልጠናውከተሳተፉየአወሊያጥበቃሰራተኞችስለሰማሁነው›› ያለውወጣትመለኩት፤ለመጅሊሱጥያቄቢያቀርቡምመጅሊሱግንለመመለስባለመቻሉ ‹‹መጅሊስአይወክለንም!›› ወደሚልጥያቄመዛወራቸውንምአስረድቷል፡፡

ወጣት መለኩት ከዳኛው ለቀረቡለት ጥያቄዎችም ምላሽ በመስጠት ምስክርነቱን አጠናቋል፡፡

ዳኛው ምስክር የመስማት ሂደቱ እስከ ሰኔወርም ድረስ ቢፈጅ እንኳ እስኪያልቅ ጊዜ ተወስዶ የሚቀጥል መሆኑን በውሳኔው አሳውቀው ችሎቱን መስጋታቸውን ያመለከተው ድምጻችን ይሰማ፤የሐሰት ከስ አይገዛንም!ትግላችን እስከ ድል ደጃፎች ይቀጥላል! ብሎአል።