የሙስሊሙ ተቃውሞ የእሁድ ሐምሌ ፰ (ስምንት) ፳፻፬ ዓ/ም ውሎ

ሐምሌ  ፰ ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:- ዛሬ ከጥዋቱ 2:30 ጀምሮ  ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ማህበረሰብ በአንዋር መስጊድ መሰባሰብ የጀመሩ ሲሆን የፌደራል ፖሊስ በየመስጊዶቹ ዙሪያውን አድፍጦ  በመጠባበቅ ላይ ይገኛል::

ይህን ዜና በምናጠናቅርበት ጊዜ ዘጋቢያችን በአንዋር መስጊድ ዙሪያ  እየቃኝ ሲሆን በብዙ መቶ ሺ የሚቆጠር ህዝብ መርካቶ በሚገኘው አንዋር መስጊድ፤ በመስገዲ ውስጥ፤ በቅጥራ ጊቢው፤ ከጊቢው ውጭ ዙሪያውን እስከ ራጉኤል ቤተ ክርስቲያን ፤ በሲኒማ ራስ አሜሪካን ጊቢ አስፋልቱን ሁሉ ሞልቶ በፌደራል ፖሊስ ተከቦ በመስገድ ላይ ይገኛል::

የህዝቡን መበራከት ያስተዋለው የኢህአዴግ መንግስት በአካባቢው መብራትና  የስልክ ኔትወርክ ያጠፋ ሲሆን መሳሪያ የታጠቁ ስናይፐሮች  (አልሞ ተኮሽ ወታደሮች)  በአንዋር መስጊድ ዙሪያ  በሚገኙ ህንፃዎች ላይ ገና በጥዋቱ  በ 12:00 ሰዓት ላይ ከህንፃዎቹ አናት ተፈናጠው በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ::

ዘጋቢያችን ተዘዋውሮ  እንደተመለከተው በአለም ተስፋ ሆቴል ህንፃ፤  በይርጋ ሀይሌ የገበያ  ማዕከል ህንፃ፤ ንግድ ባንክ አባ ኮራን ቅርንጫፍ ህንፃ እና ከአንዋር ህንፃ ፊት ለፊት በሚገኘው መድህን ህንፃ አናት ላይ ሆነው ህዝቡን ይቆጣጠራሉ::

በተጨማሪ በመስጊድ አቅራቢያ  በአራተኛ  ፖሊስ ጣቢያ  በኡመር  ስመተር ትምህርት ቤት በመያዳይ ትምህርት ቤት ቅጥር ጊቢ ጊዚያዊ የወታደር ጣቢያ  በማቋቋም በስፍራው የፌደራል ፖሊስ ተከማችቶ  በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝ ለማየት ችሏል::

በመስጊድ ዙሪያ  በራጉኤል ቤተ ክርስቲያን እና  በመስጊድ የሴቶች መግቢያ  ባለው መተለለፊያ  መንገድ ሴቶች ብቻ እንጂ ወንዶች እንዳይተላለፉ ከልክሏል::  በተለይ ክርስቲያኖ ች ከሆ ኑ ለምን ተልኮ  በዚህ መንገድእንደመጡ ሲመረመሩ ዘጋቢያችን ተመክልቷል:: በርከት ያሉ የደህንነት ሰዎች እና  ሲቪል የለበሱ ፖሊሶች እና  የኢህአዴግ ካድሬዎች ዙሪያውን አጥለቅልቀውታል:: ድንገት ሰው እየያዙ ይመረምራሉ:: የመጅሊስ አባላትም አብረዋቸው በመስራት ላይ ይገኛሉ:: ፒያስ በሚገኘው ቤኒ ኑር መስጊድ በፖሊሶች የተከበበ ሲሆን ፣ አዲሱ ሚካኤል አጠገብ ያለውም መስጊድ በፖሊሶች መከበቡን ዘጋቢያች ተመልክቶል :: ሰው ወደ አንዋር መስጊድ በመሄዱ ብዙ ሰው የላቸውም::

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide