የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ።

የመንግስት ባለስልጣናትን ሃብት በመጪው መስከረም ወር ለህዝብ_በይፋ እንደሚያሳውቅ የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ናስታወቀ።
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 11 ቀን 2010 ዓ/ም )የፌደራል ስነ-ምግባር እና ፀረ-ሙስና ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ እዬልኝ ሙሉ ዓለም እንደገለጹት
የኮሚሽኑ ተግባር ሀብትን መመዝገብ ብቻ ሳይሆን ፣ ሹመኛው ወይም ሠራተኛው ያስመዘገበው ሀብት ትክክል ነው? ወይስ አይደለም?የሚለው መረጋገጥ ጭምር እንደሆነ በመጥቀስ፤ መዝግቦ እና ማጣራት አድርጎ ያረጋጠውን ሀብት ለሕዝቡ በግልጽ ይፋ ማድረግ በአዋጅ የተደነገገ ተግባሩ መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ ኮሚሽነርቱ ገለጻ፣ ህዝቡ በመንግስት ሥልጣን ላይ ያሉ እና የመንግስት ሠራተኞች የሆኑ ሰዎችን ሀብት የማወቅ መብት አለው። ባለሥልጣናቱና ተሻሚዎቹ ከገቢያቸው በላይ ከፍተኛ ሀብት አፍርተው ሲገኙ ለፍርድ ማቅረብ ከኮሚሽኑ ተልእኮዎች መካከል አንዱ ነው።
ይህ ሀብትን አጣርቶ በይፋ ማሳወቅ በሁለት መንገድ ጠቃሚ መሆኑን ኮሚሽነሩ ያስረዳሉ። የመጀመሪያ ጠቀሜታው በሀሰት ሀብት ሳይኖራቸው እንዳላቸው ሲወራባቸው በነበሩ ተሿሚዎች ዙሪያ ያለውን እውነታ ግልጽ በማድረግ በአመራሮቹና በሕዝቡ መካከል የነበረውን ጥርጣሬ ማጥፋት ሲሆን፣ሁለተኛ ጠቀሜታው ደግሞ ሀብትን በማከማቸትና በመደበቅ የተጋለጠን አመራር ሕዝቡ እንዲታገለው ይረዳል።
በዚህ መሰረት በመጀመሪያው ዙር የተደረገውና ሹመኞች ላይ ያነጣጠረው የሀብት ምዝገባና ቁጥጥር የፊታችን መስከረም ይፋ እንደሚሆን ያስታወቁት ኮሚሽነሩ፣ በሁለተኛው ዙር ደግሞ የመንግስት ሠራተኞችን ሀብት የመመዝገቡና የማሳወቁ ሥራ እ4ንደሚቀጥል አሳውቀዋል።
የባለሥልጣናቱን ሀብት በኮሚሽኑ ድረ ገጽ ይፋ ለማድረግ ከአንድ የህንድ ድርጅት ጋር እየሠሩ መሆናቸውን ያመለከቱት ኮሚሽነሩ፣ ይህ ካልተሳካ ራሱን የቻለ መጽሔት እንደሚያዘጋጁ አስታውቀዋል።