ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ ከባድ የጦር መሳሪያዎች እየተጓጓዙ ነው።

ታኀሳስ ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት፤ ታህሳስ 26- 2007  ዓመተ ምህረት  ጧት እና ምሽት ላይ  በርካታ ታንኮችን እና ከባድ  ብረት ለበስ የጦር ተሽከርካሪዎችን ወደ ሰሜን ኢትዮጰያ አጓጉዟል።

ከየት ቦታ እንደተነሱ ያልታወቁትና ወደ ሰሜን አቅጣጫ ያመሩት ታንኮች፤ ምሽት ላይ ወልዲያ ከተማ ማረፋቸውን  ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። መንግስት ከሰሜን አካባቢ ጥቃት ሊሰነዘርብኝ ይችላል የሚል ግምገማ ማካሄዱን ኢሳት መዘገቡ ይታወሳል።